You are currently viewing የክረምት የሕዋ ሥልጠና | Summer Space Training

የክረምት የሕዋ ሥልጠና | Summer Space Training

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይስን ሶሳይቲ በሥነፈለክ ፣ የሕዋ ምህንድስና እና የኤሮስፔስ ምህንድስና ዘርፍ ለ9 ቀናት ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ላሉ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረውን ሥልጠና አጠናንቀቀ።

በመረሃ ግብሩ ከ250 በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች የተሳተፉ ሲሆን ፡ ሥልጠናው በዋነኝነት ተግባር ተኮር የሆኑ ፤ ሳይንሱን በይበልጥ በታዳጊዎች እና ወጣቶች ላይ ማስረጽ የሚችሉ ገለፃዎችን አጠቃሏል። ከዚህም ባሻገር የሥነ ፈለክ ክፍለ ግዜያት በምናባዊ እውነታ (Virtual Reality) በመደገፍ የአጽናፈ ሰማይ እና የሥርዓተ ፀሐይ ሞዴልን ለሠልጣኖች ማሳየት ተችሏል። 

ሥልጠናው በመጨረሻዎቹ ሁለት ቀናት ሠልጣኞች የተማሩትን ቀድሞ ከነበራቸው የሳይንስ ዕውቀት ጋር በማጣመር በሥነ ፈለክ ፣ ሕዋ ምህንድስና እና ኤሮስፔስ ምህንድስና የትምህርት ዓይነቶች ያዘጋጇቸውን ይዘቶች አቅርበዋል።

በመዝጊያው ዕለትም የተመረጡ ሠልጣኞች በመዝጊያው ሥነ-ስርዓት ለተገኙ ታዳሚዎች በሥልጠናው ወቅት ያገኙትን ዕውቀት አቅርበዋል። የመዝጊያ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ኢንጂነር እና አስትሮ ፊዚሲስት ነብዩ ሱሌይማን ስለ ሕዋ ሳይንስ ጥቅም እና ምንነት ለታዳሚዎቹ ጠለቅ ያለ ገለፃን ሰጥተዋል።

ሥልጠናው ከመዝጊያ ሥነ-ስርዓቱ በተጨማሪ በስፔስ ሳይስን እና ጂዖስፓሻል ኢንስቲትዩት ስር በሚተዳደረው የእንጦጦ ዖብዘርዛቶሪ እና ምርምር ማዕከል የመስክ ጉብኝት የተካሄደ ሲሆን ፤ ሠልጣኞች በጉብኝቱ በእንጦጦ ዖብዘርቫቶሪ የሚገኙትን ሁለት ኦፕቲካል ቴሌስኮፖች እንዲሁም ኢንስቲትዩቱ ከሳተላይቶች ውሂብ ለመቀበል የሚጠቀምባቸውን የሳተላይት ዳታ መቀበያ ዲቾች እና ማዕከሎች ለመጎብኘት ችለዋል። በጉብኝቱ ወቅት ለስፔስ ሳይንስ እና ጂዖስፓሻል ኢንስቲትዩት እና ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ለሠልጣኞቹ ስለ ማዕከሉ እና ማዕከሉ ውስጥ ስለሚገኙት መሣሪያዎች እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ሰፋ ያለ መግለጫን ሰጥተዋል። 

የክረምት የሕዋ ሥልጠና መረሃግብር በየዓመቱ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚካሄድ ፤ በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የተቀረጸ ፕሮጀክት ሲሆን በ2016 ዓ.ም. ብቻ በአዲስ አበባ ፣ ሐሮማያ ፣ እና ሐዋሳ ከ1,100 በላይ ተማሪዎች በሥነ ፈለክ ፣ ሕዋ ምህንድስና እና ኤሮስፔስ ምህንድስና መሠረታዊ ዕውቀቶችን ማስጨበጥ ችሏል።

The Ethiopian Space Science Society has successfully completed a 9-day training program in Astronomy, Space Engineering, and Aerospace Engineering for students ranging from primary to university levels.

Over 250 trainees participated in this hands-on training, designed to make science more accessible to teenagers and young adults. A highlight of the training was the use of virtual reality, which allowed participants to explore detailed models of the universe and the solar system, enhancing their understanding of astronomical concepts.

In the final two days, trainees synthesized their newly acquired knowledge with their previous science education, preparing and presenting slides on astronomy, space engineering, and aerospace engineering. At the closing ceremony, selected trainees showcased their presentations to the audience. The ceremony featured a detailed talk by engineer and astrophysicist Nebiyu Suleiman, who discussed the benefits and nature of space science.

Additionally, the program included a field visit to the Entoto Observatory and Research Center, which is part of the Space Science and Geospatial Institute. Trainees toured the observatory’s two optical telescopes and the satellite data receiving facilities. Experts from both the Space Science and Geospatial Institute and the Ethiopian Space Science Society provided briefings on the center’s equipment, new technologies, and operations.

The Summer Space Training Program, organized annually by the Ethiopian Space Science Society (ESSS), is held in Addis Ababa and various regional cities. This year alone, over 1,100 students in Addis Ababa, Haromaya, and Hawassa have gained foundational knowledge in astronomy, space engineering, and aerospace engineering through this initiative.